በአማርኛ   English
ቅድመ ገጽ    |    ስለ ድርጅታችን     |    የአገልግሎት ሽፋን    |    ስልጠና     |    ፕሮጀክቶች    |    አድራሻ    
Amharic
  English  
 
RUHE LONG AND FLAT PRODUCTS CONSULTANCY PLC
 
 
       
  SEARCH
RUHE LONG AND FLAT PRODUCTS CONSULTANCY PLC RUHE LONG AND FLAT PRODUCTS CONSULTANCY PLC RUHE LONG AND FLAT PRODUCTS CONSULTANCY PLC RUHE LONG AND FLAT PRODUCTS CONSULTANCY PLC RUHE LONG AND FLAT PRODUCTS CONSULTANCY PLC
     
 
NAVIGATIONS
 
 
b1
b1
b1
b1
b1
b1
b1
b1
 
 

 

ስለ ድርጅታችን - ሩሔ የረጃጅም እና የዝርግ ምርቶች አማካሪ ኃ.የተ.የግ.ማህበር!

የሩሄ የረጃጅም እና የዝርግ ምርቶች አማካሪ ኃ.የተ.የግ.ማኀበር
አጭር ፕሮፋይል

  • ራዕይ
    በረጃጅም እና በዝርግ ምርቶች የኢንዱስትሪ አማካሪነት ዘርፍ በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ተመራጭነትን መጎናፀፍ !!!
    ተልዕኮ !!!
  • ተልዕኮ
    የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሙያዎችን በመጠቀም ለረጃጅም እና ዝርግ ምርት አምራች ኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ የሆኑ የዳይ ዲዛይን፣ የምርት ፍተሻ፣ የማሽን ተከላ፣ የጥገና፣ የቴክኒክ ስልጠና፣ የአዋጭነት፣ የማስፋፊያ ጥናት፣ እንዲሁም መሰል አገልግሎቶችን በጥራት ማቅረብ፡፡
ሩሄ የረጃጅም እና የዝርግ ምርቶች አማካሪ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የረጃጅም እና ዝርግ ምርቶች አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ በልዩ ሁኔታ አተኩሮ የኢንዱስትሪ ማስፋፈያ ጥናት፣ የስራ ላይ ስልጠና፣ ጥገና፣ የምርት ልማት ጥናት፣ የማሽን ዲዛይን፣ የዳይ ዲዛይንና ማስፈብረክ፣ የተከላ ፣የሰው ኃይል አደረጃጀት ጥናት ፣እና ሌሎች መሠል አገልግሎቶችን ለመስጠት የተቋቋመ የኢንዱስትሪ እና የሥራ አመራር አማካሪ ድርጅት ነው፡፡

በአገራችን እየታየ ያለውን ወቅታዊ የኢንዱስትሪ ዘርፍ እድገትን ተከትሎ በሌሎች አገራት እንደተለመደው ሁሉ ልዩ ትኩረታቸውን በተወሠኑ የኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፎች ላይ ብቻ በማነጣጠር ብቃት ያለው አገልግሎት ለመሥጠት ራሣቸውን ያዘጋጁ የኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅቶች እንደሚያስፈለጉ ፅኑ እምነት በሰነቁ ከፍተኛ ባለሙያዎች አማካኝነት በመጋቢት ወር 2002 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተመሠረተ፡፡

ከትምህርት ዝግጅትም አንፃር፣ ከኮሌጅ ዲፕሎማ እስከ ፒ.ኤች.ዲ (ሶስተኛ ዲግሪ) እና በተለያየ ሙያ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያላቸው ባለሙያዎች የሚገኙበት አዲስ ተቋም ሲሆን ራሱን በልዩ ልዩ መንገድ እያደራጀም ይገኛል፡፡

የተመሠረተበት ጊዜ ምንም እንኳ አጭር ቢሆንም እስከ ዛሬ ድረስ በርካታ የኢንዱስትሪ ጥናቶችን እና የጥገና አገልግሎቶችን ለደንበኞቹ በተሳካ ሁኔታ እየሠጠ ይገኛል፡፡

 

 
   ቅድመ ገጽ    |    ስለ ድርጅታችን    |    አድራሻ
   © 2010 Ruhe Consultancy PLC.
 
Designed By: Hosthabesha.com